=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ሸይጧን የጅኖች ወይም የአጋንት አንዱ አካል ሲሆን የራሳቸው የሆነ አለም ወይም መኖሪያ አላቸው። እራሳቸውን ከሰው ልጅ እይታ ከመሰወር ብቃት ጋር የተፈጠሩም ናቸው።
ሸይጧን እራሱን እንደ ሰው ልጆች ሁሉ የሚያበዛ ሲሆን የራሱ የሆኑም ዘሮች አሉት።
«መላኢካዎችንም ለአደም ስገዱ ባልን ጊዜ የነበረውን አስታውስ። ለአደም ስገዱ አልን ኢብሊስ ሲቀር ሰገዱ። ከጅኖችም መካከል ነበር። የጌታውንም ትእዕዛዝ አሻፈረኝ አለ። እናም ከኔ ይልቅ ሸይጧንና ዘሮቹ ጠላቶቻችሁ ሆነው እያለ ጠባቂና ረዳት አድርጋችሁ ትይዛላችሁን?»{ሱረቱል ካኽፍ 18:50}
በዚህ መንገድ የሸይጧን ዘሮችና ተከታዮቹ የሰውን ልጅ ለማሳሳትና ትኩረቱን አለማዊ(ምደራዊ) እንዲያደርግ ይለፋሉ።
ዋና አላማው የሰው ልጆችን በማጥመም ሙሉ በሙሉ በአሏህ ላይ ያመፁ ማድረግ ነው። በእምነታቸው ጠንካራ ከሆኑበት በፈጠራዎችና በፍልስፍናዎች የተዘፈቁ እንዲሆኑ በማድረግና የአሏህን ህግጋቶች ችላ እንዲሉና እንዲቀናንሱ በማድረግ ይጀምራል።
=<({አል-ቁርአን 6 : 142})>=
«አሏህ ያስገኛችሁን ነገር ተመገቡ፤ የሸይጧንንም የእግር ኮቴ አትከተሉ፤ በእርግጥ እሱ ለእናንተ ግልፅ ጠላት ነው።»
ሸይጧን ሰለባዎቹን የሚቀርብበት መንገድ እንደ ሰው ልጆች ፍላጐትና ዝንባሌ ይለያያል። ኡለማዎችን በኡለማዎች ያጠቃል መሃይሞችን በመሃይማን ያጠቃል።
በዚህ መንገድ ሰለባውን በቀላል መንገድ ያታልለዋል። የተከለከሉ ነገሮች ሐላል ናቸው ብሎ ንዲያምን ያደርገዋል። ይህ ዘዴው ከተሳካለት ስራዎቹ ቀጣይነት ይኖራቸው ዘንድ ሹክ ይለዋል። የበለጠ ይሰራና ይታገል ዘንድ ሊያሳምነው ይሞክራል። እንዲሁም የሚሰራው ስራ በቂ አለመሆኑን ምኞቱ ሰፊና ትልቅ መሆን እንዳለበት ይነግረዋል። ትልቅ ወንጀሎችን ባትሰራ አንዳንድ ትንንሽ ወንጀሎችን የሚሠሩ ሞልተዋል ሲል ያስተምረዋል።
ሃይማኖታዊ ግዴታዎች በተለያየ መልኩ እንዲያከናውን ለማድረግ መሰናክሎችን እንዲጋፈጥ ያደርገዋል። ለምሳሌ:
=<({አል-ቁርአን 38:82-83})>=
«ኢብሊስም አለ: በሃያልነትህ ይሁንብኝ ሁሉንም አሳስታቸዋለሁ የተመረጡ ባሮችህ ሲቀሩ።»
=<({አል-ቁርአን 16:99})>=
«በእርግጥ እሱ (ሸይጧን) በነዚያ ባመኑትና ተስፋቸውንም በጌታቸው ላይ ባደረጉት ሃይል የለውም።»
=<({አል-ቁርአን 7 : 200})>=
«ከሸይጧንም በኩል ጉትጐታ ቢያጋጥምህ በአሏህ ተጠበቅ። በእርግጥ እሱ ሁሉን አዋቂ ሁሉን ሰሚ ነው።»
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|